Tuesday, September 27, 2016

ጃኪ ጎሲ እየቀለድክ መሆን አለበት

ጃኪ ጎሲ እየቀለድክ መሆን አለበት
(ተሺቲ ደዋኖ ከአርሲ)
ሰው የፈለገውን የመሆን መብት አለው:: ስር ዓቱን መደገፍም አለመደገፍም ይችላል:: አርቲስትም ቢሆን ከፈለገ ከገዳዮች ጋር ካልፈለገም ከሕዝብ ጋር መቆም ይችላል:: ግን ዘፋኝ ተነስቶ የሕዝብን አቅጣጫ ማስቀየሪያና መጠቀሚያ ሲሆን ግን ያናድዳል:: ስለዚህም የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ::
ዛሬ በአንዳንድ የወያኔ ድረገጾች ላይ የጃኪ ጎሲ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቆ አየሁ:: ትናንት በሊቢያ ወገኖቻቸን ሲገደሉ በነጋታው ነጠላ ዜማ የለቀቀው ጃኪ ዛሬ በኦሮሚኛ አንድ ነጠላ ዜማ ለቀቀ ሲሉኝ በጣም ተደስቼ ዘፈኑን ከፍቼ ተመልከትኩት:: ጃኪ በኦሮሚኛ ዘፈን መስራቱ የሚደነቅ ቢሆንም የኦሮሞ ወጣቶች በየቀኑ እያለቁ እርሱ ግን ለምን በኦሮሚኛ የሰለቸንን ስለሴት ልጅ ፍቅር ዘፈን ሊዘፍንልኝ ቻለ? ስል ጥያቄ ውስጤ ጫረ::
ይህን ያልኩት ከጃኪ የተሻለ ሥራ ጠብቄ አይደለም:: ዘፈን ለመስረቅ አስመራ ዘፋኞች ድረስ የሚሄደው ይኸው ድምጻዊ ወደ ኦሮሚኛ ዘፈን ፊቱን ሲያዞር በኦሮሞ ልጆች ግድያ ዙሪያ ይዘፍናል ብዬ ትንሽ አስቤ ነበር:: ተስፋ የጣልኩበትም ምክንያት ባለፈው በሊቢያ ጉዳይ ተንደርድሮ ሰው እንዳይቀድመው ነጠላ ዜማ መስራቱን አይቼ ነው::
ሆኖም ግን በወያኔ ድረገጾች በኩል የተለቀቀው ይኸው የጃኪ አዲስ የኦሮሚኛ ሙዚቃ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት አቅጣጫ ለማስቀየርና አንዳንድ ሃገር ወዳድ የኦሮሚኛ; የጉራጊኛ እና የአማርኛ ሙዚቃ አርቲስቶች በሃገራቸውና በወገኖቻቸው ግድያ ዙሪያ መንግስትን ተው አትግደል ያሉባቸውን ዘፈኖች ለማዳፈን ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑ ይታመናል:: ለዚህም ነው ጃኪ በዚህ ወቅት የፍቅር ዘፈን በኦሮሚኛ መልቀቁን አይቼ እየቀለድክ መሆን አለበት ያልኩት::
ጃኪ የሊቢያ ወገኖቻችን መሞት እውነት አሳዝኖህ እንዳልዘፈንክ ዛሬ በኦሮሚኛ ዘፈንህ ላይ አሳይተኸናል:: ያኔ ያንን ነጠላ ዜማ የለቀቅከው በወገኖቻችን ሞት አንተ ዝናን ለማግኘት እንደተጠቀምክበት ነው የምቆጥረው:: ለወገንህ የምታዝን ቢሆን ኖሮ በአማራ ክልል ይህ ሁሉ ወጣት ሲሞት; በኦሮሚያ ግድያው በተጠናከረበት ወቅት እንዲህ ያለውን ልፍስፍስ ዘፈን ለቀህ የወያኔ መጠቀሚያ አትሆንም ነበር:: Read more here

No comments:

Post a Comment