ሕወሃትና ብአዴን በትግራይና በአማራ ክልል ያሉ የወሰን ችግሮችን በቅርቡ ይፈታሉ--- ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ
በአማራና በትግራይ ክልሎች የሚታዩ የወሰን ችግሮችን ህወሃትና ብአዴን በቅርቡ እንደሚፈቱት የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ገለጹ።
የኢህአዴግ ምክር ቤት ሰሞኑን ባስተላለፈው ውሳኔና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተነሳው የወሰን ማካለል ሥራ በሀገሪቱ ሕገ-መንግስት መሰረት የሚፈታ ነው።
ይሔንንና ሌሎች ችግሮች በማንሳት በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጠሩት ሁከቶች መነሻቸው የጸረ-ሰላም እና ጸረ-ዲሞክራሲ አመለካከት መሆኑንም ተናግረዋል።
ችግሮቹ የስርዓቱ ዋንኛ አደጋ መሆናቸው በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብስባ ላይ መለየታቸውን ገልጸው በአባል ድርጅቶችና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተቀናጀ ተሳትፎ እንደሚፈቱም አመልክተዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ሽፋን በማድረግ በዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ምንጩ ሕዝብ ሳይሆን ስርዓቱን በሚጠሉ ጸረ-ሰላም ኃይሎች መሆኑንም ተናግረዋል።
"ችግሩ እንዲቆም ሕወሃት የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል" ያሉት ርዕሰ-መስተዳደሩ የጥፋቱ ስፋትና ጥልቀት እየተጠና መሆኑንም ጠቁመዋል።
ምንጭ፡ ኢዜአ/መቀሌ ነሃሴ26/2008
No comments:
Post a Comment