Thursday, September 1, 2016

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኮንሶ መዘጋታቸውን የክልሉ መንግሥት አመነ

ኮንሶ
በኮንሶ ከልዩ ወረዳነት ወደ ሰገን ዞን መጠቃለላቸውን የተቃወሙ የመንግሥት ሠራተኞችና የህብረተሰቡ ወኪሎች የመንግሥት ሥራ ያቆሙትና ደመወዝም አልቀበልም ያሉት በራሳቸው ፍላጎት እንደሆነ የደቡብ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
ነዋሪዎችና ወኪሎቻቸው ከ50 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላትን አዋቅረው፣ ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ፤ እስካሁን ተገቢውን ምላሽ አለማግኘቱና ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።
በኮንሶ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እንደማይሰጡ፣ ጤና ጣቢያዎችም ጭምር መዘጋታቸውን ለደሃ ደሃ የሚሰጠው የምግብ ዋስትና መቋረጡን ጭምር ይገልፃሉ።
የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በዞን እንጠቃለል ለሚለው ጥያቄ ተገቢው ምላሽ መሰጠቱን ገልፀው መንግሥት መስሪያ ቤቶችን አልዘጋም፤ ጥያቄያችን ተቀባይነት ከሌለው አንሰራም ብለው የቀሩት ሠራተኞቹ ናቸው ይላሉ።
የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ የሕገ-መንግስት ባለሞያንም አነጋግሯል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።  Read more or lissen here

No comments:

Post a Comment