Saturday, May 25, 2013

ተዝቆ ተዝቆ የማያልቅ ተፍቆ ተፍቆ የማይለቅ ተጨምቆ ተጨምቆ የማይደርቅ የእሷ ፍቅር ከማር በላይ ማር ድንቅ ናት ድንቅ የሩቅ መንገድ ስንቅ ብርቅ ናት ብርቅ ከወርቅ በላይ ወርቅ ታስቀይም ይሆናል በሆነ ምክንያት እሷም ትቀየም ይሆናል በሆነ ምክንያት ሆኖም ዞሮ ዞሮ እምዬ ናት እናት

No comments:

Post a Comment